ሐሰት፡ የትግራይ ቲቪ እና ህወሓት ያወጧቸው ምስሎች ሐሰተኛ ናቸው | Fact-check

ሐሰት፡ የትግራይ ቲቪ እና ህወሓት ያወጧቸው ምስሎች ሐሰተኛ ናቸው | Fact-check

ሐሰት፡ የትግራይ ቲቪ እና ህወሓት ያወጧቸው ምስሎች ሐሰተኛ ናቸው

ህወሓት (ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ) በይፋዊ የፌስቡክ ገጹ በኩል ዛሬ (ህዳር 2፣2014 አ/ም) “ጀግናው የትግራይ ሰራዊት በሚሌ ግንባር የጦር ሄሊኮፕተርን መጣሉን አስታወቀ” በሚል ከታች የሚታየውን ምስል አጋርቷል

በተመሳሳይ የትግራይ ቴሌቭዥን በይፋዊ ፌስቡክ ገጹ በኩል ይሄንኑ መረጃ በትግርኛ ቋንቋ ከሌላ ምስል ጋር ለጥፏል

አዲስ ሚዲያ በሃቅ ማንጠሪያ ክፍሉ በኩል ከኮድ ፎር አፍሪካ ጋር በመተባበር ከዘገባዎቹ ጋር ተያይዘው በቀረቡት ሁለት ምስሎች ላይ የማጣራት ስራ ያከናወነ ሲሆን በዚህም ሐሰተኛ መሆናቸውን አረጋግጧል።

በማጣራት ሂደቱ አዲስ ሚዲያ የጉግል ምስል ማሰሻን (Google reverse image search) የተጠቀመ ሲሆን ፥ ህወሓት በይፋዊ የፌስቡክ ገጹ “…የትግራይ ሰራዊት በሚሌ የጦር ሄሊኮፕተር መጣሉን አስታወቀ” ከሚል መረጃ ጋር ያጋራው ምስል በጎርጎሮሲያኑ የዘመን አቆጣጠር በ 2016 በኢራቅ የነበረውን ሁኔታ በተመለከተ የእንግሊዙ ዘታይም ድረ-ገጽ የተጠቀመው መሆኑን አመላክቷል

በሌላ በኩል የትግራይ ቴሌቭዥን የተጠቀመው…

Read The Full Article – Click Here

See More Latest Ethiopian News on AddisMedia.net

Fact-check: ሳፋሪኮም የቴሌግራም ቻናሉን ለሚቀላቀሉ 12ሺ ሰዎች ሽልማት አዘጋጅቷል?

Fact-check: ሳፋሪኮም የቴሌግራም ቻናሉን ለሚቀላቀሉ 12ሺ ሰዎች ሽልማት አዘጋጅቷል?

ሐሰት፡ ሳፋሪኮም “የቴሌግራም ቻናሉን ለሚቀላቀሉ ሽልማት አዘጋጅቷል” በሚል የተሰራጨው መረጃ ሐሰተኛ ነው

በኢትዮጵያ የቴሌኮም ዘርፍ ለመሰማራት የተደረገውን ጨረታ ከሌሎች አለም አቀፍ ተቋማት ጋር በጥምረት አሸናፊ በሆነው በኬንያው ሳፋሪኮም ኩባንያ ስምና አርማ የተከፈተ “Safaricom Ethiopiaየተባለ የቴሌግራም ቻናል “ሳፋሪኮም ቻናሉን እስከ ጥቅምት 15 ለሚቀላቀሉ 12ሺ ሰዎች በተለያየ መጠን የድምጽ እና ኢንተርኔት ጥቅል እንዲሁም የገንዘብ ሽልማት አዘጋጅቷል” የሚል መረጃ አሰራጭቷል።

አዲስ ሚዲያ በሃቅ ማንጠሪያ ክፍሉ በኩል ከኮድ ፎር አፍሪካ ጋር በመተባበር በቴሌግራም ቻናሉ በተሰራጨው መረጃ ላይ ዳሰሳ አድርጓል።

የቴሌግራም ቻናሉ ነሐሴ 2 ፣ 2012 (August 8, 2020) የተከፈተ ሲሆን ሳፋሪኮምን የተመለከቱ መረጃዎች ማሰራጨት የጀመረው ከመስከረም 25 ፣ 2014 (October 25, 2021) ነው።

በተደረገው የማጣራት ስራም ከዚህ በታች የሚገለጹትን ግኝቶች ዋቢ በማድረግ ቻናሉ ሐሰተኛ መሆኑ ተረጋግጧል።

  1. በኬንያው ሳፋሪኮም ኩባንያ የሚመራው ጥምረት በኢትዮጵያ የቴሌኮም ዘርፍ የወጣውን ጨረታ በ850 ሚሊየን ዶላር አሸናፊ…

Read The Full Article – Click Here

See More Latest Ethiopian News on AddisMedia.net

Fact-Check: አልጀዚራ በቲውተር ገጹ የለጠፈው ምስል አሳሳች ነው

Fact-Check: አልጀዚራ በቲውተር ገጹ የለጠፈው ምስል አሳሳች ነው

አሳሳች፡ የፌደራል ጦር በዚህ ሳምንት በመቀሌ የአየር ጥቃት መፈጸሙን ተከትሎ አልጀዚራ በቲውተር ገጹ የለጠፈው ምስል የደረሰውን ጉዳት የማያመለክትና አሳሳች መሆኑ ተረጋግጧል።

አልጀዚራ (Al Jazeera English) በይፋዊ የቲውተ ገጹ ላይ በጥቅምት 8 ፣ 2014 (እ.ኤ.አ October 18, 2021) “የኢትዮጵያ መከላከያ ኃይል በትግራይ ክልል ዋና ከተማ የአየር ጥቃት መፈጸሙን ተከትሎ ቢያንስ 3 ሰዎች ተገደሉ” የሚል መረጃ ከአንድ ምስል ጋር አጋርቷል

አዲስ ሚዲያ ከኮድ ፎር አፍሪካ ጋር በመተባበር በምስሉ ላይ ባካሄደው ዳሰሳ አልጀዚራ በቲውተር ገጹ ለሰራው ዘገባ የተጠቀመው ምስል አሳሳች የሆነና ሰሞነኛውን ጥቃት ተከትሎ በመቀሌ የደረሰውን ጉዳት የሚያመላክት አለመሆኑን አረጋግጧል።

በዚህም መሰረት ምስሉ ሰኔ 17 ፣ 2013 አ/ም (እ.ኤ.አ June 24, 2021) በትግራይ በምትገኘው ቶጎጋ መንደር በተፈጸመ የአየር ጥቃት እግሯ ላይ ጉዳት የደረሰባት የ 13 አመት ታዳጊ በመቀሌ አጠቃላይ ሆስፒታል የህክምና እርዳታ እየተደረገላት የሚያሳይ ሲሆን ምስሉ በፈረንሳይ ዜና አገልግሎት (AFP)  የፎቶ ባለሙያ ያሱዮሺ ቺባ የተነሳ ነው

በመሆኑም አልጀዚራ…

Read The Full Article – Click Here

See More Latest Ethiopian News on AddisMedia.net