ሐሰት፡ የላሊበላ ከተማ በህወሃት ቁጥጥር ስር አይደለችም

Oromo Liberation Army” የሚል  ስያሜ ያለው ከ1ሺ800 በላይ ተከታዮች ያሉት የቲውተር ገጽ “በሰሜን ኢትዮጵያ እየተካሄደ ባለው ጦርነት የትኞቹ ቦታዎች በማን እንደተያዙ የሚያሳይ የሳተላይት ምስል” በማለት ህዳር 22 ፣ 2014 አ/ም (December 1, 2021) በለጠፈው የካርታ ምስል እና መረጃ ላሊበላ በህወሃት ታጣቂዎች ስር እንደምትገኝ ገልጿል

አዲስ ሚዲያ  ከኮድ ፎር አፍሪካ ጋር በመተባበር የተለያዩ ማስረጃዎችን ዋቢ በማድረግ የላሊበላ ከተማ አሁን ላይ በህወሃት ታጣቂዎች ቁጥጥር ስር አለመሆኗን አረጋግጧል።

ትላንት አመሻሹን የላሊበላ ከተማ በመከላከያ ሰራዊት እና አጋር ሃይሎች ቁጥጥር ስር መግባቷ ተዘግቧል

ሮይተርስ የዜና ምንጭ የላሊበላ ከተማ በፌደራልና አጋር የክልል ሃይሎች ቁጥጥር ስር መዋሏን በተመለከተ በሰራው ዘገባ ፥ የህወሃት ታጣቂዎች ከተማዋን ለቀው መውጣታቸውን ከአካባቢው ነዋሪዎች ማረጋገጡን ይፋ አድርጓል

The post ሐሰት፡ የላሊበላ ከተማ በህወሃት ቁጥጥር ስር አይደለችም appeared first on Addis Media.

Read The Full Article – Click Here

See More Latest Ethiopian News on AddisMedia.net