Fact-Check: አልጀዚራ በቲውተር ገጹ የለጠፈው ምስል አሳሳች ነው

Fact-Check: አልጀዚራ በቲውተር ገጹ የለጠፈው ምስል አሳሳች ነው

አሳሳች፡ የፌደራል ጦር በዚህ ሳምንት በመቀሌ የአየር ጥቃት መፈጸሙን ተከትሎ አልጀዚራ በቲውተር ገጹ የለጠፈው ምስል የደረሰውን ጉዳት የማያመለክትና አሳሳች መሆኑ ተረጋግጧል።

አልጀዚራ (Al Jazeera English) በይፋዊ የቲውተ ገጹ ላይ በጥቅምት 8 ፣ 2014 (እ.ኤ.አ October 18, 2021) “የኢትዮጵያ መከላከያ ኃይል በትግራይ ክልል ዋና ከተማ የአየር ጥቃት መፈጸሙን ተከትሎ ቢያንስ 3 ሰዎች ተገደሉ” የሚል መረጃ ከአንድ ምስል ጋር አጋርቷል

አዲስ ሚዲያ ከኮድ ፎር አፍሪካ ጋር በመተባበር በምስሉ ላይ ባካሄደው ዳሰሳ አልጀዚራ በቲውተር ገጹ ለሰራው ዘገባ የተጠቀመው ምስል አሳሳች የሆነና ሰሞነኛውን ጥቃት ተከትሎ በመቀሌ የደረሰውን ጉዳት የሚያመላክት አለመሆኑን አረጋግጧል።

በዚህም መሰረት ምስሉ ሰኔ 17 ፣ 2013 አ/ም (እ.ኤ.አ June 24, 2021) በትግራይ በምትገኘው ቶጎጋ መንደር በተፈጸመ የአየር ጥቃት እግሯ ላይ ጉዳት የደረሰባት የ 13 አመት ታዳጊ በመቀሌ አጠቃላይ ሆስፒታል የህክምና እርዳታ እየተደረገላት የሚያሳይ ሲሆን ምስሉ በፈረንሳይ ዜና አገልግሎት (AFP)  የፎቶ ባለሙያ ያሱዮሺ ቺባ የተነሳ ነው

በመሆኑም አልጀዚራ…

Read The Full Article – Click Here

See More Latest Ethiopian News on AddisMedia.net