አሳሳች: BBC News “ኢትዮጵያ ጦርነትን ለማጠናከር ትምህርት ቤቶችን ዘጋች” በሚል ያሰራጨው መረጃ አሳሳች ነው

አሳሳች: BBC News “ኢትዮጵያ ጦርነትን ለማጠናከር ትምህርት ቤቶችን ዘጋች” በሚል ያሰራጨው መረጃ አሳሳች ነው

አሳሳች: BBC “ኢትዮጵያ ጦርነትን ለማጠናከር ትምህርት ቤቶችን ዘጋች” በሚል ያሰራጨው መረጃ አሳሳች ነው

ግዙፉ አለም አቀፍ የዜና ተቋም ቢቢሲ “BBC News (world) በተባለው እና ከ 33 ሚሊየን በላይ ተከታዮች ባሉት የቲውተር ገጹ በኩል “ኢትዮጵያ የእርስ በርስ ጦርነትን ለማጠናከር ትምህርት ቤቶችን ዘጋች ” የሚል መረጃ አሰራጭቷል

አዲስ ሚዲያ በሃቅ ማንጠሪያ ክፍሉ በኩል ባካሄደው የማጣራት ስራ መረጃው ሐሰተኛ እና አሳሳች መሆኑን አረጋግጧል።

የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ከተቋሙ ሌሎች አመራሮች ጋር ህዳር 23 ፣ 2014 (December 2, 2021) በሰጡት መግለጫ “በሀገር አቀፍ ደረጃ የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች ፣ መምህራን እና ሰራተኞች ከህዳር 27 እስከ ታህሳስ 3፣ 2014 ለአንድ ሳምንት ያልተሰበሰቡ የዘማች ሰብሎችን እንዲሰበስቡ እንዲሁም ቤተሰቦቻቸውንም እንዲረዱ መደበኛ ትምህርት እንዲቋረጥ ተወስኗል” ሲሉ ይፋ አድርገዋል

ቢቢሲ በቲውተር ገጹ “ትምህርት ቤቶች እንዲዘጉ” ሲል የገለጸበት  ሁኔታ ሐሰተኛ እና አሳሳች ሲሆን ከላይ እንደተገለጸው ለአንድ ሳምንት ብቻ ትምህርት እንዲቋረጥ…

Read The Full Article – Click Here

See More Latest Ethiopian News on AddisMedia.net

አሳሳች፡ “የትህነግ ደጋፊዎች ቤተክርስቲያን መሳሪያ ሊቀብሩ ሲሉ ተያዙ” በሚል የተሰራጨው ምስል ሐሰተኛ ነው

አሳሳች፡ “የትህነግ ደጋፊዎች ቤተክርስቲያን መሳሪያ ሊቀብሩ ሲሉ ተያዙ” በሚል የተሰራጨው ምስል ሐሰተኛ ነው

አሳሳች፡ “የትህነግ ደጋፊዎች ቤተክርስቲያን መሳሪያ ሊቀብሩ ሲሉ ተያዙ” በሚል የተሰራጨው ምስል ሐሰተኛ ነው

‘Abonesh Abera Gutema’ የሚል ስያሜ ያለው ከ8ሺ በላይ ተከታዮች ያሉት የቲውተር ገጽ ሕዳር 1፣ 2014 አ/ም (November 10, 2021) “የሽብርተኛው ትህነግ ደጋፊዎች ተክለ ተይማኖት /ቤተ ክርስቲያን አስክሬን አስመስለው መሳሪያ ሊቀብሩ ሲሉ ተያዙ” የሚል መረጃ ከአንድ ምስል ጋር አጋርቷል

መረጃው በተለቀቀ በጥቂት ጊዜ ውስጥ ከ780 ጊዜ በላይ ሪትዊት ሲደረግ ከ1100 በላይ ላይክ አግኝቷል። ከትዊተር በተጨማሪ ፌስቡክ ላይ ሼር ተደርጎ ብዙ ሰዎች ግብረ መልስ ሰጥተውበት ተመልክተናል።

አዲስ ሚዲያ በሀቅ ማንጠሪያ ክፍሉ በኩል ከኮድ ፎር አፍሪካ ጋር በመተባበር በምስሉ ትክክለኛነት ላይ የማጣራት ስራ አከናውኗል። በዚህም ምስሉ ከመረጃው ጋር የማይዛመድ እና አሳሳች መሆኑን አረጋግጧል።

የጉግል ምስል ማሰሻ (Google reverse image search) ምስሉ ከስምንት አመታት በፊት ጥቅምት 21፣2006 አ/ም (October 31, 2013)  ‘Tincanbandit’ በተባለ ጦማር ጥቅም ላይ መዋሉን ያሳያል

በመሆኑም “የትህነግ ደጋፊዎች ቤተክርስቲያን አስክሬን አስመስለው…

Read The Full Article – Click Here

See More Latest Ethiopian News on AddisMedia.net

Fact-Check: አልጀዚራ በቲውተር ገጹ የለጠፈው ምስል አሳሳች ነው

Fact-Check: አልጀዚራ በቲውተር ገጹ የለጠፈው ምስል አሳሳች ነው

አሳሳች፡ የፌደራል ጦር በዚህ ሳምንት በመቀሌ የአየር ጥቃት መፈጸሙን ተከትሎ አልጀዚራ በቲውተር ገጹ የለጠፈው ምስል የደረሰውን ጉዳት የማያመለክትና አሳሳች መሆኑ ተረጋግጧል።

አልጀዚራ (Al Jazeera English) በይፋዊ የቲውተ ገጹ ላይ በጥቅምት 8 ፣ 2014 (እ.ኤ.አ October 18, 2021) “የኢትዮጵያ መከላከያ ኃይል በትግራይ ክልል ዋና ከተማ የአየር ጥቃት መፈጸሙን ተከትሎ ቢያንስ 3 ሰዎች ተገደሉ” የሚል መረጃ ከአንድ ምስል ጋር አጋርቷል

አዲስ ሚዲያ ከኮድ ፎር አፍሪካ ጋር በመተባበር በምስሉ ላይ ባካሄደው ዳሰሳ አልጀዚራ በቲውተር ገጹ ለሰራው ዘገባ የተጠቀመው ምስል አሳሳች የሆነና ሰሞነኛውን ጥቃት ተከትሎ በመቀሌ የደረሰውን ጉዳት የሚያመላክት አለመሆኑን አረጋግጧል።

በዚህም መሰረት ምስሉ ሰኔ 17 ፣ 2013 አ/ም (እ.ኤ.አ June 24, 2021) በትግራይ በምትገኘው ቶጎጋ መንደር በተፈጸመ የአየር ጥቃት እግሯ ላይ ጉዳት የደረሰባት የ 13 አመት ታዳጊ በመቀሌ አጠቃላይ ሆስፒታል የህክምና እርዳታ እየተደረገላት የሚያሳይ ሲሆን ምስሉ በፈረንሳይ ዜና አገልግሎት (AFP)  የፎቶ ባለሙያ ያሱዮሺ ቺባ የተነሳ ነው

በመሆኑም አልጀዚራ…

Read The Full Article – Click Here

See More Latest Ethiopian News on AddisMedia.net