አሳሳች፡ “የትህነግ ደጋፊዎች ቤተክርስቲያን መሳሪያ ሊቀብሩ ሲሉ ተያዙ” በሚል የተሰራጨው ምስል ሐሰተኛ ነው
‘Abonesh Abera Gutema’ የሚል ስያሜ ያለው ከ8ሺ በላይ ተከታዮች ያሉት የቲውተር ገጽ ሕዳር 1፣ 2014 አ/ም (November 10, 2021) “የሽብርተኛው ትህነግ ደጋፊዎች ተክለ ተይማኖት /ቤተ ክርስቲያን አስክሬን አስመስለው መሳሪያ ሊቀብሩ ሲሉ ተያዙ” የሚል መረጃ ከአንድ ምስል ጋር አጋርቷል።
መረጃው በተለቀቀ በጥቂት ጊዜ ውስጥ ከ780 ጊዜ በላይ ሪትዊት ሲደረግ ከ1100 በላይ ላይክ አግኝቷል። ከትዊተር በተጨማሪ ፌስቡክ ላይ ሼር ተደርጎ ብዙ ሰዎች ግብረ መልስ ሰጥተውበት ተመልክተናል።
አዲስ ሚዲያ በሀቅ ማንጠሪያ ክፍሉ በኩል ከኮድ ፎር አፍሪካ ጋር በመተባበር በምስሉ ትክክለኛነት ላይ የማጣራት ስራ አከናውኗል። በዚህም ምስሉ ከመረጃው ጋር የማይዛመድ እና አሳሳች መሆኑን አረጋግጧል።
የጉግል ምስል ማሰሻ (Google reverse image search) ምስሉ ከስምንት አመታት በፊት ጥቅምት 21፣2006 አ/ም (October 31, 2013) ‘Tincanbandit’ በተባለ ጦማር ጥቅም ላይ መዋሉን ያሳያል።
በመሆኑም “የትህነግ ደጋፊዎች ቤተክርስቲያን አስክሬን አስመስለው…
Read The Full Article – Click Here
See More Latest Ethiopian News on AddisMedia.net