መንግስት ተገዶ ወደ ጦርነት ገብቷል | ከአቶ አባዱላ ጋር የተደረገ ቃለ መጠይቅ

መንግስት ተገዶ ወደ ጦርነት ገብቷል | ከአቶ አባዱላ ጋር የተደረገ ቃለ መጠይቅ



ባለፉት ሶስት አስርት ዓመታት በተለያዩ የሃገሪቱ ከፍተኛ የስልጣን እርከኖች ላይ ሲሰሩ የነበሩት አቶ አባዱላ ገመዳ ከዶይቼ ቬለ ጋር ባደረጉት ቃለመጠይቅ በፌዴራሉ እና ትግራይ ክልልን በሚያስተዳድረው “ህወሓት” መካከል የነበሩ የሃሳብ ልዩነቶች ጦር ለመማዘዝም የማያበቁ እንደነበሩ ተናግረዋል፡፡ ይሁንና ከብልጽግና ፓርቲ ምስረታ በኋላ “የሁለቱ ወገኖች ልዩነት የመጥበብ አዝማሚያን አላሳየም” ያሉት የቀድሞው ጉምቱ ባለስልጣን በተለይም ህወሓት “በፌዴራሉ መንግስትና በህገመንግስቱም ጭምር እውቅና የተነፈገ” ካሉት የትግራዩ ምርጫ በኋላ ግን ነገሮች ወዳልተፈለገ አቅጣጫ ማምራታቸውን እና የድርድር መስመርን ያጠበቡ ብለውታል፡፡ በህወሓት ባለስልጣንም ጭምር ተረጋግጧል ያሉት የሰሜን ዕዝ የሃገር መከላከያ ሰራዊት ላይ የተወሰደው ያልታሰበ ያሉት ጥቃት ደግሞ “የፌዴራሉ መንግስት ተገዶ ወደ ጦርነት ለመግባቱ ማሳያ ነው” ያሉት አቶ አባዱላ አሁን ሊደርስ የሚችለውን ቀውስ የሚያሳንሰው የጦርነቱን ጊዜ ማሳጠር ብቻ ነው ሲሉም አክለዋል፡፡

Watch daily updated Ethiopian news from a reliable and balanced source. Addis Media is an independent Ethiopian related News and other programs, producer.
Visit us https://AddisMedia.net Subscribe to our channel to follow everything related to Ethiopia.
AddisMedia Daily Ethiopian News Source #Ethiopia #EthiopianNews


Subscribe to AddisMedia Channel


AddisMeda Your Community Website.