ሐሰት፡ የላሊበላ ከተማ በህወሃት ቁጥጥር ስር አይደለችም

Oromo Liberation Army” የሚል  ስያሜ ያለው ከ1ሺ800 በላይ ተከታዮች ያሉት የቲውተር ገጽ “በሰሜን ኢትዮጵያ እየተካሄደ ባለው ጦርነት የትኞቹ ቦታዎች በማን እንደተያዙ የሚያሳይ የሳተላይት ምስል” በማለት ህዳር 22 ፣ 2014 አ/ም (December 1, 2021) በለጠፈው የካርታ ምስል እና መረጃ ላሊበላ በህወሃት ታጣቂዎች ስር እንደምትገኝ ገልጿል

አዲስ ሚዲያ  ከኮድ ፎር አፍሪካ ጋር በመተባበር የተለያዩ ማስረጃዎችን ዋቢ በማድረግ የላሊበላ ከተማ አሁን ላይ በህወሃት ታጣቂዎች ቁጥጥር ስር አለመሆኗን አረጋግጧል።

ትላንት አመሻሹን የላሊበላ ከተማ በመከላከያ ሰራዊት እና አጋር ሃይሎች ቁጥጥር ስር መግባቷ ተዘግቧል

ሮይተርስ የዜና ምንጭ የላሊበላ ከተማ በፌደራልና አጋር የክልል ሃይሎች ቁጥጥር ስር መዋሏን በተመለከተ በሰራው ዘገባ ፥ የህወሃት ታጣቂዎች ከተማዋን ለቀው መውጣታቸውን ከአካባቢው ነዋሪዎች ማረጋገጡን ይፋ አድርጓል

The post ሐሰት፡ የላሊበላ ከተማ በህወሃት ቁጥጥር ስር አይደለችም appeared first on Addis Media.

Read The Full Article – Click Here

See More Latest Ethiopian News on AddisMedia.net

ሐሰት: “የፌደራል ፖሊስ ለውጊያ ወደ ደብረብርሃን ተልኳል” በሚል የተሰራጨው ምስል ሐሰተኛ ነው

የፌደራል ፖሊስ ለውጊያ ወደ ደብረብርሃን እየተጓዘ ነው በሚል የቀረበው ምስል ሀሰተኛ ነው

“Oromo Liberation Army” የተባለ ከ1ሺ300 በላይ  ተከታዮች ያሉት የቲውተር ገጽ “…የአብይ መንግስት ለመጨረሻው  ውጊያ የፌደራል ፖሊስ አባላትን ወደ ደብረብርሃን እያጓጓዘ ነው”  በሚል አንድ ምስል አጋርቷል።

አዲስ ሚዲያ ከኮድ ፎር አፍሪካ ጋር በመተባበር ከመረጃው ጋር ተያይዞ በቀረበው ምስል ላይ የማጣራት  ስራ አከናውኗል።

በማጣራት ሂደቱ የጉግል ምስል ማሰሻን (Google reverse image search) የተጠቀምን ሲሆን ይሄም ከመረጃው ጋር አባሪ ሆኖ የቀረበው ምስል አሳሳች መሆኑን አረጋግጠናል።

በግኝቱ ምስሉ በኢትዮጵያ አቆጣጠር በነሃሴ ወር 2007 አ/ም (August  13, 2015) በፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ይፋዊ የፌስቡክ ገጽ ላይ  የተለጠፈ መሆኑ ታውቋል።

በወቅቱ የፌደራል ፖሊስ በስልጠና ላይ በነበረበት ጊዜ ምስሉ የተነሳ መሆኑንም ተመልክተናል።

በተጨማሪም በተሽከርካሪው ላይ  የሚታዩት የፌደራል ፖሊስ አባላት የለበሱት ነባሩን የተቋሙን ደንብ ልብስ መሆኑም በግልጽ ይታያል።

በዚህም መሰረት አዲስ ሚዲያ ከላይ የተጠቀሱትን…

Read The Full Article – Click Here

See More Latest Ethiopian News on AddisMedia.net

ሐሰት፡ የትግራይ ቲቪ እና ህወሓት ያወጧቸው ምስሎች ሐሰተኛ ናቸው | Fact-check

ሐሰት፡ የትግራይ ቲቪ እና ህወሓት ያወጧቸው ምስሎች ሐሰተኛ ናቸው | Fact-check

ሐሰት፡ የትግራይ ቲቪ እና ህወሓት ያወጧቸው ምስሎች ሐሰተኛ ናቸው

ህወሓት (ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ) በይፋዊ የፌስቡክ ገጹ በኩል ዛሬ (ህዳር 2፣2014 አ/ም) “ጀግናው የትግራይ ሰራዊት በሚሌ ግንባር የጦር ሄሊኮፕተርን መጣሉን አስታወቀ” በሚል ከታች የሚታየውን ምስል አጋርቷል

በተመሳሳይ የትግራይ ቴሌቭዥን በይፋዊ ፌስቡክ ገጹ በኩል ይሄንኑ መረጃ በትግርኛ ቋንቋ ከሌላ ምስል ጋር ለጥፏል

አዲስ ሚዲያ በሃቅ ማንጠሪያ ክፍሉ በኩል ከኮድ ፎር አፍሪካ ጋር በመተባበር ከዘገባዎቹ ጋር ተያይዘው በቀረቡት ሁለት ምስሎች ላይ የማጣራት ስራ ያከናወነ ሲሆን በዚህም ሐሰተኛ መሆናቸውን አረጋግጧል።

በማጣራት ሂደቱ አዲስ ሚዲያ የጉግል ምስል ማሰሻን (Google reverse image search) የተጠቀመ ሲሆን ፥ ህወሓት በይፋዊ የፌስቡክ ገጹ “…የትግራይ ሰራዊት በሚሌ የጦር ሄሊኮፕተር መጣሉን አስታወቀ” ከሚል መረጃ ጋር ያጋራው ምስል በጎርጎሮሲያኑ የዘመን አቆጣጠር በ 2016 በኢራቅ የነበረውን ሁኔታ በተመለከተ የእንግሊዙ ዘታይም ድረ-ገጽ የተጠቀመው መሆኑን አመላክቷል

በሌላ በኩል የትግራይ ቴሌቭዥን የተጠቀመው…

Read The Full Article – Click Here

See More Latest Ethiopian News on AddisMedia.net

ሐሰት፡ የቀድሞው የመቀሌ ዩኒቨርስቲ ፕሬዝዳንት ያጋሩት ምስል ሐሰተኛ ነው

ሐሰት፡ የቀድሞው የመቀሌ ዩኒቨርስቲ ፕሬዝዳንት ያጋሩት ምስል ሐሰተኛ ነው

የቀድሞው የመቀሌ ዩኒቨርስቲ ፕሬዝዳንት ፕሮፌሰር ክንደያ ገብረሕይወት ከ100ሺ በላይ ተከታዮች ባሉት የቲውተር ገጻቸው በኩል “የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት በመሐል ደሴ ከተማ ሰላማዊ ዜጎችን ለአደጋ በሚያጋልጥ ሁኔታ መድፍ ጠምዶ እየተከላከለ ነው” በሚል አንድ ምስል አጋርተዋል

አዲስ ሚዲያ በሃቅ ማንጠሪያ ክፍሉ በኩል ከኮድ ፎር አፍሪካ ጋር በመተባበር ባካሄደው የማጣራት ስራ ፕሮፌሰር ክንደያ ገብረሕይወት ያጋሩት ምስል ሐሰተኛ መሆኑን አረጋግጧል።

የአዲስ ሚዲያ ሃቅ ማንጠሪያ ቡድን የምስሉን ሐሰተኛነት ለማረጋገጥ የተለያዩ የማጣሪያ መንገዶችን የተጠቀመ ሲሆን በዚህም ምስሉ ከቪዲዮ ላይ ተቀንጭቦ የተወሰደ መሆኑና ከኢትዮጵያ ውጪ የተቀረጸ መሆኑ ተረጋግጧል

አዲስ ሚዲያ በማጣራት ሂደቱ የጉግል ካርታ (Google Map street view) በመጠቀም ቪዲዮው የተቀረጸበትን ትክክለኛ ቦታም ለይቷል

ከላይ የሚታየው የጉግል ካርታ ምስል በግልጽ በቪዲዮው መድፍ ሲተኮስ የነበረበትን ስፍራ ማለትም በደቡብ ሩሲያ በምትገኘው ኖቮስፕሪክስ ከተማ ያለውን የኦራ ገበያ ማእከል ያመላክታል።

በመሆኑም በመቀሌ…

Read The Full Article – Click Here

See More Latest Ethiopian News on AddisMedia.net

ሐሰት፡ የኖርዌይ ትምህርት ተቋም (University of Oslo) ነጻ የትምህርት ዕድል አላቀረበም

ሐሰት፡ የኖርዌይ ትምህርት ተቋም (University of Oslo) ነጻ የትምህርት ዕድል አላቀረበም

ሐሰት፡ የኖርዌይ ትምህርት ተቋም (University of Oslo) ነጻ የትምህርት ዕድል አላቀረበም

የማህበራዊ መገናኛ ዘዴ በሆነው ዋትስ አፕ በርካቶች የኖርዌይ ከፍተኛ ትምህርት ተቋም የሆነው University of Oslo የነጻ ትምህርት ዕድል ስላቀረበ አመልክቱ የሚል መልዕክት እየደረሳቸው መሆኑን ተመልክተናል።

በምስሉ ላይ እንደሚታየው “የኦስሎ ዩኒቨርስቲ መሉ በሙሉ በነጻ ያቀረበውን የ 2021 የትምህርት ዕድል (Scholarship) ተጠቃሚ ለመሆን ያመልክቱ” የሚል መግቢያ ያለው መልዕክቱ የኦስሎ ዩኒቨርስቲ ባቀረበው በዚህ የነጻ ትምህርት ዕድል (Scholarship) ሙሉ በሙሉ የትምህርት ወጪ ፣ የመኖሪያ አበል ፣ ማረፊያ ክፍል ፣ የህክምና ወጪ ፣ የጉዞ አበል እና ያልተገደበ የስራ ፍቃድ ተጠቃሚ መሆን እንደሚያስችል ያትታል።

ከዚህ በታች በምስሉ ላይ እንደሚታየው የምዝገባ ሂደቱን ካጠናቀቁ በኋላ የቪዛ ፕሮሰስ ለመጀመር ስለ ትምህርት ዕድሉ “ለ15 ጓደኞችዎ ወይም 5 የዋትስ አፕ ግሩፕ” ላይ ማጋራት ግዴታ መሆኑን ይገልጻል።

ሆኖም አዲስ ሚዲያ በሀቅ ማንጠሪያ ክፍሉ በኩል ባደረገው ማጣራት ዩኒቨርስቲ ኦፍ ኦስሎ (University of Oslo)  ምንም አይነት የነጻ…

Read The Full Article – Click Here

See More Latest Ethiopian News on AddisMedia.net