አሳሳች: BBC “ኢትዮጵያ ጦርነትን ለማጠናከር ትምህርት ቤቶችን ዘጋች” በሚል ያሰራጨው መረጃ አሳሳች ነው
ግዙፉ አለም አቀፍ የዜና ተቋም ቢቢሲ “BBC News (world) በተባለው እና ከ 33 ሚሊየን በላይ ተከታዮች ባሉት የቲውተር ገጹ በኩል “ኢትዮጵያ የእርስ በርስ ጦርነትን ለማጠናከር ትምህርት ቤቶችን ዘጋች ” የሚል መረጃ አሰራጭቷል።
አዲስ ሚዲያ በሃቅ ማንጠሪያ ክፍሉ በኩል ባካሄደው የማጣራት ስራ መረጃው ሐሰተኛ እና አሳሳች መሆኑን አረጋግጧል።
የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ከተቋሙ ሌሎች አመራሮች ጋር ህዳር 23 ፣ 2014 (December 2, 2021) በሰጡት መግለጫ “በሀገር አቀፍ ደረጃ የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች ፣ መምህራን እና ሰራተኞች ከህዳር 27 እስከ ታህሳስ 3፣ 2014 ለአንድ ሳምንት ያልተሰበሰቡ የዘማች ሰብሎችን እንዲሰበስቡ እንዲሁም ቤተሰቦቻቸውንም እንዲረዱ መደበኛ ትምህርት እንዲቋረጥ ተወስኗል” ሲሉ ይፋ አድርገዋል።
ቢቢሲ በቲውተር ገጹ “ትምህርት ቤቶች እንዲዘጉ” ሲል የገለጸበት ሁኔታ ሐሰተኛ እና አሳሳች ሲሆን ከላይ እንደተገለጸው ለአንድ ሳምንት ብቻ ትምህርት እንዲቋረጥ…
Read The Full Article – Click Here
See More Latest Ethiopian News on AddisMedia.net