ሐሰት፡ የኖርዌይ ትምህርት ተቋም (University of Oslo) ነጻ የትምህርት ዕድል አላቀረበም
የማህበራዊ መገናኛ ዘዴ በሆነው ዋትስ አፕ በርካቶች የኖርዌይ ከፍተኛ ትምህርት ተቋም የሆነው University of Oslo የነጻ ትምህርት ዕድል ስላቀረበ አመልክቱ የሚል መልዕክት እየደረሳቸው መሆኑን ተመልክተናል።
በምስሉ ላይ እንደሚታየው “የኦስሎ ዩኒቨርስቲ መሉ በሙሉ በነጻ ያቀረበውን የ 2021 የትምህርት ዕድል (Scholarship) ተጠቃሚ ለመሆን ያመልክቱ” የሚል መግቢያ ያለው መልዕክቱ የኦስሎ ዩኒቨርስቲ ባቀረበው በዚህ የነጻ ትምህርት ዕድል (Scholarship) ሙሉ በሙሉ የትምህርት ወጪ ፣ የመኖሪያ አበል ፣ ማረፊያ ክፍል ፣ የህክምና ወጪ ፣ የጉዞ አበል እና ያልተገደበ የስራ ፍቃድ ተጠቃሚ መሆን እንደሚያስችል ያትታል።
ከዚህ በታች በምስሉ ላይ እንደሚታየው የምዝገባ ሂደቱን ካጠናቀቁ በኋላ የቪዛ ፕሮሰስ ለመጀመር ስለ ትምህርት ዕድሉ “ለ15 ጓደኞችዎ ወይም 5 የዋትስ አፕ ግሩፕ” ላይ ማጋራት ግዴታ መሆኑን ይገልጻል።
ሆኖም አዲስ ሚዲያ በሀቅ ማንጠሪያ ክፍሉ በኩል ባደረገው ማጣራት ዩኒቨርስቲ ኦፍ ኦስሎ (University of Oslo) ምንም አይነት የነጻ…
Read The Full Article – Click Here
See More Latest Ethiopian News on AddisMedia.net
Get involved!
Comments