ሐሰት: “የፌደራል ፖሊስ ለውጊያ ወደ ደብረብርሃን ተልኳል” በሚል የተሰራጨው ምስል ሐሰተኛ ነው

የፌደራል ፖሊስ ለውጊያ ወደ ደብረብርሃን እየተጓዘ ነው በሚል የቀረበው ምስል ሀሰተኛ ነው

“Oromo Liberation Army” የተባለ ከ1ሺ300 በላይ  ተከታዮች ያሉት የቲውተር ገጽ “…የአብይ መንግስት ለመጨረሻው  ውጊያ የፌደራል ፖሊስ አባላትን ወደ ደብረብርሃን እያጓጓዘ ነው”  በሚል አንድ ምስል አጋርቷል።

አዲስ ሚዲያ ከኮድ ፎር አፍሪካ ጋር በመተባበር ከመረጃው ጋር ተያይዞ በቀረበው ምስል ላይ የማጣራት  ስራ አከናውኗል።

በማጣራት ሂደቱ የጉግል ምስል ማሰሻን (Google reverse image search) የተጠቀምን ሲሆን ይሄም ከመረጃው ጋር አባሪ ሆኖ የቀረበው ምስል አሳሳች መሆኑን አረጋግጠናል።

በግኝቱ ምስሉ በኢትዮጵያ አቆጣጠር በነሃሴ ወር 2007 አ/ም (August  13, 2015) በፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ይፋዊ የፌስቡክ ገጽ ላይ  የተለጠፈ መሆኑ ታውቋል።

በወቅቱ የፌደራል ፖሊስ በስልጠና ላይ በነበረበት ጊዜ ምስሉ የተነሳ መሆኑንም ተመልክተናል።

በተጨማሪም በተሽከርካሪው ላይ  የሚታዩት የፌደራል ፖሊስ አባላት የለበሱት ነባሩን የተቋሙን ደንብ ልብስ መሆኑም በግልጽ ይታያል።

በዚህም መሰረት አዲስ ሚዲያ ከላይ የተጠቀሱትን…

Read The Full Article – Click Here

See More Latest Ethiopian News on AddisMedia.net

About : AddisZena
Share Latest Ethiopian News - አዲስ ዜና

Get involved!

Get Connected! Join Now
Come and join our community. Expand your network and get to know new people!

Comments

No comments yet